ሰው ፣ የተሽከርካሪ እና የሕንጻ የመድን ዋስት ሽፋን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሰው፣የተሽከርካሪ እና የሕንጻ የመድን ዋስት ሽፋን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን  ሚያዝያ 21ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 12ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -10፡00 ድረስ “ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ” ደብረዘይት መንገድ ጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡት

  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፡፡
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ እስከ ግንቦት 13ቀን 2016 .ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 306 ማስገባት ይችላሉ፣ ጨረታው በዚሁ ቀን ግንቦት 13ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር306 የሚከፈት ይሆናል::

ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልከተኩ ተጫራቾች ወዲያውኑ ከጨረታ ውድድሩ የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0937313131/0902993161 መጠቀም ይችላሉ፡

ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                  ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር LT/HT/HO/02/2024

Recent Posts

  • All Posts
  • REOI
  • Tender Notice
  • Business
You have been successfully Subscribed! Ops! Something went wrong, please try again.

About Us

We are a private national distributor of telecom products through more than 800 shops across Ethiopia

Contact Us

© 2024 Hidaise Telecom,  Design and Developed by EYOB